የሌላውን ሰው ማዕድ በመቀላወጥ የሚገፋ ሕይወት፥ ከቶውንም ሕይወት አይባልም፤ የሌሎች ምግብ ጉሮሮን ያሳድፋል፤ ጥበበኛ የሆነና መልካም አስተዳደግ ያለው ሰው ይህን አያደርግም።
የሌላ ማዕድ ደጅ የሚጠናና ተስፋ የሚያደርግ ሰው፤ ኑሮው እንደ ሞተ ሰው ነው፤ የሰው እህል የሚወድ ሰው ከሐሜት አይድንም፤ የተመከረ ብልህ ሰው ግን ከሁሉ ይጠበቃል።