ከጥቂት ጊዜ በኋላም፥ ቦዔዝ ከቤተልሔም መጣ፥ አጫጆችንም፦ “ጌታ ከእናንተ ጋር ይሁን” አላቸው። እነርሱም፦ “ጌታ ይባርክህ” ብለው መለሱለት።
ሩት 2:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቦዔዝም በአጫጆች ላይ አዛዥ የነበረውን አገልጋዩን፦ “ይህች ብላቴና የማን ናት?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ቦዔዝ የዐጫጆቹን አለቃ፣ “ይህች ወጣት ሴት የማን ናት?” ሲል ጠየቀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ቦዔዝ የአጫጆቹ ኀላፊ የሆነውን ሰው “ያቺ ወጣት ሴት ማን ናት?” ሲል ጠየቀው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቦዔዝም በአጫጆች ላይ አዛዥ የነበረውን ሎሌውን፦ ይህች ቆንጆ የማን ናት? አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቦዔዝም በአጫጆች ላይ አዛዥ የነበረውን ሎሌውን “ይህች ወጣት ሴት የማን ናት?” አለው። |
ከጥቂት ጊዜ በኋላም፥ ቦዔዝ ከቤተልሔም መጣ፥ አጫጆችንም፦ “ጌታ ከእናንተ ጋር ይሁን” አላቸው። እነርሱም፦ “ጌታ ይባርክህ” ብለው መለሱለት።