ሩት 1:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጆቼ ሆይ፥ ተመለሱ፥ ባል ለማግባት አርጅቻለሁና ሂዱ፥ ተስፋ አለኝ ብል፥ ዛሬ ሌሊትስ እንኳ ባል ባገባ፥ ወንዶች ልጆችም ብወልድ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደየቤታችሁ ተመለሱ፣ ልጆቼ፤ ሌላ ባል እንዳላገባ እጅግ አርጅቻለሁ፤ አሁንም ተስፋ አለኝ ብል፣ ዛሬ ማታ አግብቼ ከዚያም ልጆች ብወልድ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጆቼ ሆይ! ወደየቤታችሁ ተመለሱ፤ እኔ ሌላ ባል እንዳላገባ ዕድሜዬ አይፈቅድልኝም፤ ለመሆኑ ለማግባት ተስፋ ቢኖረኝና ዛሬውኑ አግብቼ ልጆች ብወልድስ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጆቼ ሆይ፥ ተመለሱ፣ ባል ለማግባት አርጅቻለሁና ሂዱ፣ ተስፋ አለኝ ብል፥ ዛሬ ሌሊትስ እንኳ ባል ባገባ፥ ወንዶች ልጆችም ብወልድ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልጆቼ ሆይ! ተመለሱ፤ ባል ለማግባት አርጅቻለሁና ሂዱ፤ ተስፋ አለኝ ብል፥ ዛሬ ሌሊትስ እንኳ ባል ባገባ፥ ወንዶች ልጆችም ብወልድ፥ |
ከዚያም ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን፥ “ልጄ ሴሎም ለአካለ መጠን እስኪደርስ ድረስ ወደ አባትሽ ቤት ሄደሽ መበለት ሆነሽ ብትኖሪ ይሻላል” አላት፤ ይህን ያለውም፥ ሴሎም እንደ ወንድሞቹ ተቀሥፎ ይሞትብኛል ብሎ ስለ ሠጋ ነበር። ትዕማርም እንዳላት ሄደች፤ በአባቷም ቤት ተቀመጠች።
እነርሱ እስኪያድጉ እስኪደርሱ መጠበቅ ትችላላችሁን? በእነርሱስ ምክንያት ባል ሳታገቡ ትቆያላችሁን? ልጆቼ ሆይ፥ እንዲህስ አይሆንም፥ እኔን ጌታ ተቈጥቶኛል፤ በእናንተም ላይ በደረሰው ነገር በጣም አዝኜአለሁ።”