ሮሜ 7:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ የማልፈልገውን ነገር የማደርግ ከሆነ ሕግ ትክክል ነው እላለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማድረግ የማልፈልገውን የማደርግ ከሆነ፣ ሕጉ በጎ እንደ ሆነ እመሰክራለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ እኔ የማደርገው የማልፈልገውን ነገር ከሆነ ሕግ መልካም እንደ ሆነ እመሰክራለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የማልወደውን የምሠራ ከሆንሁ ግን ያ የኦሪት ሕግ መሠራት ለበጎ እንደ ሆነ ምስክሩ እኔ ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማልወደውን ግን የማደርግ ከሆንሁ ሕግ መልካም እንደ ሆነ እመሰክራለሁ። |