La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሮሜ 7:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንግዲህ መልካም የሆነው ነገር ሞት ሆነብኝን? በጭራሽ! ነገር ግን ኃጢአት ኃጢአትነቱ እንዲታይ፥ መልካም በሆነው ነገር ሞትን ይሠራብኝ ነበር። ይኸውም ኃጢአት በትእዛዝ አማካይነት ያለ ልክ ኃጢአት እንዲሆን ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ታዲያ በጎ የሆነው ነገር ሞት ሆነብኝን? ከቶ አይሆንም! ነገር ግን ኀጢአት በኀጢአትነቱ ይታወቅ ዘንድ በጎ በሆነው ነገር በኩል ሞትን አመጣብኝ፤ ይኸውም ኀጢአት በትእዛዝ በኩል ይብሱን ኀጢአት ይሆን ዘንድ ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ታዲያ፥ ይህ መልካም የሆነው ነገር በእኔ ሞትን አመጣብኝ ማለት ነውን? አይደለም! ነገር ግን ኃጢአት፥ ኃጢአት ሆኖ እንዲገለጥ በመልካሙ ነገር አማካይነት ሞትን አመጣብኝ፤ ስለዚህ ኃጢአት በትእዛዝ አማካይነት የበለጠ ኃጢአተኛ ሆነ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ግ​ዲህ ያ መል​ካም ነው ብዬ የማ​ስ​በው ነገር በውኑ አጥፊ ሆነኝ እላ​ለ​ሁን? አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ኀጢ​አት ኀጢ​አት እንደ ሆነች በታ​ወ​ቀች ጊዜ ሞትን አበ​ዛ​ች​ብኝ፤ ከዚ​ያም ትእ​ዛዝ የተ​ነሣ ኀጢ​አ​ተ​ናው እን​ዲ​ታ​ወቅ፥ ኀጢ​አ​ትም ተለ​ይታ እን​ድ​ት​ታ​ወቅ ኦሪት መል​ካ​ሙን ከክፉ ልት​ለይ ተሠ​ር​ታ​ለች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንግዲህ በጎ የሆነው ነገር ለእኔ ሞት ሆነብኝን? አይደለም፥ ነገር ግን ኃጢአት ሆነ፤ ኃጢአትም በትእዛዝ ምክንያት ያለ ልክ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ ኃጢአትም እንዲሆን ይገለጥ ዘንድ በጎ በሆነው ነገር ለእኔ ሞትን ይሠራ ነበር።

Ver Capítulo



ሮሜ 7:13
7 Referencias Cruzadas  

በፍርሃትና በታላቅ ደስታ ፈጥነው ከመቃብሩ ሄዱ፤ ለደቀ መዛሙርቱም ሊነግሩ ሮጡ።


ይመጣል እነዚህንም ተከራዮች ያጠፋል፥ የወይኑንም አትክልት ለሌሎች ይሰጣል።” ይህንንም በሰሙ ጊዜ “ይህስ በጭራሽ አይሁን፤” አሉ።


በደል እንዲበዛ ሕግ ገባ፤ ነገር ግን ኃጢአት በበዛበት፥ ጸጋ ይበልጥ በዛ፤


ሕግ ከሥጋ ድካም የተነሣ ማድረግ ያልቻለውን፥ እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌና ስለ ኃጢአት ልኮ ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ፤


እንግዲህ ሕግ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ይቃወማልን? በጭራሽ አይደለም። ሕይወትን ሊሰጥ የሚችል ሕግ ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ በእርግጥ ጽድቅ በሕግ በኩል በሆነ ነበር፤