ሮሜ 5:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በደል እንዲበዛ ሕግ ገባ፤ ነገር ግን ኃጢአት በበዛበት፥ ጸጋ ይበልጥ በዛ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕግ በመምጣቱ መተላለፍ በዛ፤ ነገር ግን ኀጢአት በበዛበት ጸጋ አብልጦ የተትረፈረፈ ሆነ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአት ይበዛ ዘንድ ሕግ መጣ፤ ነገር ግን ኃጢአት በበዛ መጠን የእግዚአብሔር ጸጋ በይበልጥ በዛ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኦሪትስ ኀጢአትን ታበዛት ዘንድ መጣች፤ ኀጢአትም ከበዛች ዘንድ የእግዚአብሔር ጸጋ በዛች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በደልም እንዲበዛ ሕግ ጭምር ገባ፤ ዳሩ ግን ኃጢአት በበዛበት፥ ኃጢአት በሞት እንደ ነገሠ፥ እንዲሁ ደግሞ ጸጋ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣ በጽድቅ ምክንያት ለዘላለም ሕይወት ይነግሥ ዘንድ፥ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በለጠ። |
አንቺም ደግሞ ለእኅቶችሽ ስለ ፈረድሽ እፍረትሽን ተሸከሚ፥ ከእነርሱ የባሰ ኃጢአት ሠርተሻልና ከአንቺ ይልቅ ጻድቃን ናቸው፥ እኅቶችሽንም ስለ አጸደቅሻቸው እፈሪ እፍረትሽንም ተሸከሚ።