ሮሜ 3:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “መልካም ነገር እንዲመጣ ለምን ክፉ አናደርግም?” ይላሉ ብለው እንደሚያሙን አይደለም፤ የሚፈረድባቸው ፍርድ ትክክለኛ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህማ “በጎ እንዲመጣ ክፉ እንሥራ” ይላሉ በማለት አንዳንዶች እንደሚያስወሩብን ነው፤ በእነዚህ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ፍርድ ትክክለኛ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዳንድ ሰዎች “መልካም ነገር እንድናገኝ ክፉ ነገር እናድርግ” እያልኩ የማስተምር አስመስለው ይከሱኛል፤ ስለዚህ እንዲህ ባሉት ላይ የሚፈረድባቸው ፍርድ ትክክለኛ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኑ እና መልካም ነገር እናገኝ ዘንድ ክፉ ነገር እናድርግ እንደምንል አስመስለው የሚጠረጥሩንና የሚነቅፉን ሰዎች እንደሚሰድቡን ነን? ለእነርሱስ ቅጣታቸው ተዘጋጅቶላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ምንስ መልካም እንዲመጣ ክፉ አናደርግም? እንዲሁ ይሰድቡናልና አንዳንዱም እንዲሁ እንድንል ይናገራሉና። የእነርሱም ፍርድ ቅን ነው። |
እንግዲህ ምን እንላለን? ሕግ ኃጢአት ነውን? በጭራሽ! ነገር ግን በሕግ በኩል ባይሆን ኖሮ ኃጢአትን አላውቅም ነበር፤ ሕጉ “አትመኝ” ባይል ኖሮ ምኞትን አላውቅም ነበር።
አስቀድሞ ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በዝሙት ይለውጣሉ፤ ብቸኛ ንጉሣችንና ጌታችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።