ሮሜ 16:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኬንክሪየስ ቤተ ክርስቲያን ዲያቆን የሆነችውን እኅታችንን ፊቢንን አደራ ብያችኋለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በክንክራኦስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆነችውን እኅታችንን ፌቤንን ዐደራ እላችኋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፌቤ በክንክሪያ ከተማ ቤተ ክርስቲያንን የምታገለግል ታማኝ እኅታችን መሆንዋን እንድታውቁ እወዳለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለክንክራኦስ ቤተ ክርስቲያን የምትላላከውን እኅታችንን ፌቤንን አደራ እላችኋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በክንክራኦስ ባለች ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የምትሆን እኅታችንን ፌቤንን አደራ ብያችኋለሁ፤ |
አሁን በዚህ ዘመን ከስደት ጋር ቤቶችን፥ ወንድሞችን፥ እኅቶችን፥ እናቶችን፥ ልጆችንና ዕርሻን መቶ ዕጥፍ የማይቀበል፥ በሚመጣውም ዓለም የዘለዓለም ሕይወት የማይወርስ የለም።
ከዚህም በኋላ ጳውሎስ እጅግ ቀን ተቀምጦ ወንድሞችንም ተሰናብቶ በመርከብ ወደ ሶርያ ሄደ፤ ስለትም ነበረበትና ራሱን በክንክራኦስ ተላጨ፤ ጵርስቅላና አቂላም ከእርሱ ጋር ነበሩ።
እንደገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ አንዳንዶች እንደሚያደርጉት ለእናንተ ወይም ከእናንተ የተጻፈ የምስጋና ደብዳቤ ያስፈልገን ይሆንን?