የሚያምን ሁሉ እንዲጸድቅ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና።
ለሚያምን ሁሉ ጽድቅ ይሆን ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና።
ሰው ሁሉ በእምነት እንዲጸድቅ ሕግ በክርስቶስ አክትሞአል።
የኦሪት ጽድቅ ፍጻሜስ ለሚያምኑበት ሁሉ በክርስቶስ ማመን ነው።
የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና።
ከነፍሱ ሥቃይ ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ አገልጋዬ በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፤ ኃጢአታቸውንም ይሸከማል።
ለሚቃጠልም መሥዋዕት አንድ ወይፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት፤
ኢየሱስ ግን “እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና ለአሁን ፍቀድልኝ፤” ሲል መለሰለት፥ ያንጊዜ ፈቀደለት።
ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።
ይህ የእግዚአብሔር ጽድቅ ለሚያምኑ ሁሉ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ባለን እምነት የሚገኝ ነው፤ ልዩነት የለምና፤
ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፥ ጽድቃችንና ቅድስናችንም ቤዛችንም በተደረገልን፥ በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።
ስለዚህ በእምነት እንድንጸድቅ፥ ሕግ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ ሞግዚታችን ሆነ፤
ይህም ከሕግ በታች ያሉትን ለመዋጀት፥ እኛም ልጅነትን እንድናገኝ ነው።
የአለቅነትና የሥልጣን ሁሉ ራስ በሆነ በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል።
እነዚህ ወደ ፊት ለሚመጡት ነገሮች እንደ ጥላ ናቸውና፤ እውነቱ የሚገኘው ግን በክርስቶስ ነው።
ምክንያቱም አንድ ጊዜ ራሱን መሥዋዕት በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋል።