ሮሜ 1:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ደግሞ ወንዶች ተፈጥሮአዊ የሆነውን ከሴት ጋር መገናኘት ትተው እርስ በእርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም ከወንዶች ጋር ነውር ፈጸሙ፤ በስሕተታቸውም ምክንያት የሚገባቸውን ቅጣት በራሳቸው ላይ ተቀበሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደዚሁም ወንዶች ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወት ተቃጠሉ፤ ወንዶች ከወንዶች ጋራ ነውር ፈጸሙ፤ በዚህም ጥፋታቸው በገዛ ራሳቸው የሚገባቸውን ቅጣት ተቀበሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ወንዶቹ የተለመደውን ግንኙነት ከሴቶች ጋር ማድረግ ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ስለዚህ ወንዶች ከወንዶች ጋር አሳፋሪ ነገር ፈጸሙ፤ በስሕተታቸውም ምክንያት የሚገባቸውን ቅጣት በሥጋቸው ይቀበላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንዶችም እንዲሁ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን ትተው በፍትወት ተቃጠሉ፤ እርስ በርሳቸውም እየተመላለሱ፥ ወንዶች በወንዶች ላይ የሚያዋርዳቸውን ነውር ሠሩ፤ ነገር ግን ፍዳቸውን ያገናሉ፤ ፍዳቸውም በራሳቸው ይመለሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። |
ወይስ ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? አትሳሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆኑ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ፥
እንዲሁም ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች፥ እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ በዘለዓለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።