አቤቱ፥ ጸሎቴን አድምጥ፥ የልመናዬንም ድምፅ ስማ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን አድምጥ፤ የልመናዬን ጩኸት ስማ።
እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ፤ የልመናዬንም ጩኸት አድምጥ።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ፥ በውስጥዋም ለተወለዱት አለቆችዋ በመጽሐፍ ይነግራቸዋል።
ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባርያህን ጸሎት፥ ስምህን በመፍራት የሚደሰቱትን የባርያዎችህን ጸሎት ያድምጥ፤ ዛሬ ለባርያህ እባክህን አከናውንለት፥ በዚህም ሰው ፊት ሞገስን ስጠው። እኔም የንጉሡ ጠጅ አሳላፊ ነበርኩ።
አቤቱ፥ ድምፄን ስማ፥ ጆሮህ የልመናዬን ቃል ያድምጥ።
የዳዊት ጸሎት። አቤቱ፥ ጽድቄን ስማ ጩኸቴንም አድምጥ፥ ተንኰል ከሌለበት ከንፈር የሚወጣውንም ጸሎቴን አድምጥ።
ለመዘምራን አለቃ፥ በበገናዎች፥ የዳዊት ትምህርት።