አምላኬ፥ ከክፉ እጅ፥ ከዓመፀኛና ከግፈኛም እጅ አድነኝ።
አምላኬ ሆይ፤ ከክፉ እጅ፣ ከግፈኛና ከጨካኝ መዳፍ አውጣኝ።
አምላኬ ሆይ! ከክፉ ኀይልና ርኅራኄ ከሌለው ዐመፀኛ እጅ አድነኝ።
ለድሆች ሕዝብህ በጽድቅ ፍረድ፥ የድሆችንም ልጆች አድናቸው። ትዕቢተኛውንም አዋርደው።
ሰዎቹ ከሄዱ በኋላ ሁለቱም ከጉድጓዱ ወጥተው ሄዱ፤ ለንጉሥ ዳዊትም፥ “አኪጦፌል በአንተ ላይ እንዲህ እንዲህ ብሎ ስለመከረብህ ተነሥተህ በፍጥነት ወንዙን ተሻገር” አሉት።
አቤቱ፥ ተነሥ፥ ቀድመህ ወደ ታች ጣለው፥ ነፍሴን ከኃጢአተኛ በሰይፍህ አድናት።
አቤቱ፥ ፍረድልኝ፥ ከጽድቅ በራቁም ሕዝብ ዘንድ ተሟገትልኝ፥ ከሸንጋይና ከግፈኛ ሰው አድነኝ።