አለቆች ቀደሙ፥ መዘምራንም ተከተሉ፥ ከበሮን በሚመቱ በቈነጃጅት መካከል።
እግዚአብሔርን በጉባኤ አመስግኑት፤ ከእስራኤል ምንጭ የተገኛችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑ።
እነርሱም፦ “በሕዝቡ ጉባኤ መካከል አምላክን አመስግኑ! በእስራኤል ጉባኤ መካከል እግዚአብሔርን አመስግኑ!” ይላሉ።
አንተ የቀሠፍኸውን እነርሱ ተከትለዋልና፥ በቍስሌም ላይ ቍስልን ጨመሩብኝ።
በሕዝብ ጉባኤ መካከል ከፍ ከፍ ያድርጉት፥ በሽማግሌዎችም ሸንጎ ያመስግኑት።
ሃሌ ሉያ! በቅኖች ሸንጎ በጉባኤም ጌታን በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ።
እግሮቼ በቅንነት ቆመዋልና፥ አቤቱ፥ በማኅበር አመሰግንሃለሁ።
በአንቺ የሚኖሩ ሁሉ ደስ እንደሚላቸው ይነግራቸዋል።
የአሮን እኅት ነቢይቱ ማሪያምም ከበሮ በእጅዋ ወሰደች፤ ሴቶችም ሁሉ ከበሮ በመያዝና በጭፈራ በኋላዋ ወጡ።
ምንጮችህ ወደ ሜዳ፥ ወንዞችህ ወደ አደባባይ ይፈስሳሉን?
እናንተ በእስራኤል ስም የተጠራችሁ ከይሁዳም ውኆች የወጣችሁ፥ በጌታ ስም የምትምሉ፥ በእውነት ሳይሆን በጽድቅም ሳይሆን የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩ፥
እስራኤልም ተማምኖ፥ የያዕቆብም ምንጭ ብቻውን፥ እህልና የወይን ጠጅ ባለባት ምድር ይኖራል፥ ሰማያትም ጠልን ያንጠባጥባሉ።