“አንተን በማሳዘናቸው ምክንያት ዝናብ እንዳይዘንብላቸው አድርገህ በምትቀጣቸው ጊዜ፥ በፈጸሙት በደል በመጸጸት ፊታቸውን ወደዚህ ቤተ መቅደስ መልሰው በትሕትና ቢለምኑህ፥
መዝሙር 5:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐሰትን የሚናገሩትን ታጠፋቸዋለህ፥ ደም አፍሳሹንና ሸንጋዩን ሰው ጌታ ይጸየፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ አንተንም በመፍራት፣ ወደ ተቀደሰው መቅደስህ እሰግዳለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ግን በታላቅ ምሕረትህ ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ ወደ ቤተ መቅደስህ በአክብሮት እሰግዳለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ አንተን በመፍራት በቤተ መቅደስህ እሰግዳለሁ። |
“አንተን በማሳዘናቸው ምክንያት ዝናብ እንዳይዘንብላቸው አድርገህ በምትቀጣቸው ጊዜ፥ በፈጸሙት በደል በመጸጸት ፊታቸውን ወደዚህ ቤተ መቅደስ መልሰው በትሕትና ቢለምኑህ፥
ልብን የሚያሸብር መራር ኀዘን ደርሶባቸው፥ ከማንም ሰው ወይም ከሕዝብህ እስራኤል ወደዚህ ቤተ መቅደስ እጃቸውን በመዘርጋት በሚጸልዩበት ጊዜ፥
ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፥ ስለ ጽኑ ፍቅርሀና ስለ ታማኝነትህ ስምህንም አመሰግናለሁ፥ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህንና ቃልህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና።
ከዚያም በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመልሰው አምላካቸውን ጌታንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤ በኋለኛውም ዘመን ፈርተው ወደ ጌታና ወደ መልካምነቱ ይመጣሉ።
በይሁዳም ሁሉና በገሊላ በሰማርያም የነበሩት አብያተ ክርስቲያናት በሰላም ኖሩ፤ ታነጹም፤ በእግዚአብሔርም ፍርሃትና በመንፈስ ቅዱስ መጽናናት እየሄዱ ይበዙ ነበር።
ጌታንም ማገልገል ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥ አባቶቻችሁ በወንዝ ማዶ ሳሉ ያገለገሉአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው የተቀመጣችሁባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታገለግሉ እንደሆነ፥ የምታገለግሉትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን ጌታን እናገለግላለን።”