እግዚአብሔርን፦ አንተ መጠጊያዬ ነህ፥ ለምን ረሳኸኝ? ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን አዝኜ እመላለሳለሁ? እለዋለሁ።
ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ፣ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ፣ በነገር ጠዘጠዙኝ፣ ዐጥንቴም ደቀቀ።
ጠላቶቼ “ሁልጊዜ አምላክህ የት አለ?” ብለው በሚያላግጡብኝ ጊዜ አጥንቶቼ እንኳ ይታመማሉ።
ነፍሴ እግዚአብሔርን፥ ሕያው አምላክን ተጠማች፥ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?
አንተ አምላኬ ኃይሌም፥ ለምን ትተወኛለህ? ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን አዝኜ እመላለሳለሁ?
ከጠላት ድምፅ ከዓመፀኛም ግፍ የተነሣ፥ ዓመፃን በላዬ ጥለውብኛልና፥ በቁጣም ጠልተውኛልና።
እንደሚዋጋ ሰይፍ የሚለፈልፍ ሰው አለ፥ የጠቢባን ምላስ ግን ጤና ነው።
ስለምን ለዘለዓለም ትረሳናለህ? ስለ ምንስ ለረጅም ዘመን ትተወናለህ?
የጌታም አገልጋዮች ካህናት ከወለሉና ከመሠዊያው መካከል እያለቀሱ፦ “አቤቱ፥ ለሕዝብህ ራራ፥ አሕዛብም እንዳይነቅፉአቸው ርስትህን ለማላገጫ አሳልፈህ አትስጥ፤” ከአሕዛብ መካከል፦ “አምላካቸው ወዴት ነው?” ስለምን ይበሉ?
ጠላቴም ታያለች፥ “ጌታ አምላክህ የት ነው?” ያለችኝን ኀፍረት ይከድናታል፥ ዐይኖቼ ያዩአታል፤ አሁን እንደ መንገድ ጭቃ ትረገጣለች።
በዚህም የብዙዎችን የልባቸውን አሳብ የሚገለጥ ይሆናል፤ በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል።”