እኔ ብቸኛና የተጨነቅሁ ነኝና ፊትህን ወደ እኔ መልስ ማረኝም።
እኔ ብቸኛና የተጨነቅሁ እንደ መሆኔ፣ ወደ እኔ ተመለስ፤ ምሕረትም አድርግልኝ።
እኔ ብቸኛና ችግረኛ ስለ ሆንኩ አምላክ ሆይ! ወደ እኔ ተመለስ፤ በጎነትንም አድርግልኝ።
እኔ ችግረኛ ምስኪንም ነኝና፥ በውስጤም ልቤ ቆስሎአል።
ስምህን ለሚወድዱ እንደምታደርገው ፍርድ፥ ወደ እኔ ተመልከት ማረኝም።
ነፍሴ በውስጤ አለቀችብኝ፥ ልቤም በውስጤ ደነገጠብኝ።
ኃጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ፥ በደሌንም አልሸፈንሁም፥ መተላለፌን ለጌታ እነግራለሁ አልሁ፥ አንተም የኃጢአቴን ሸክም ተውህልኝ።
ለመዘምራን አለቃ፥ ለትምህርት የዳዊት ቅኔ።
የዳዊት ጸሎት አቤቱ፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አድምጠኝም፥ ደሃና ችግረኛ ነኝና።
ወደ እኔ ተመልከት፥ ራራልኝ፥ ኃይልህን ለአገልጋይህ፥ ማዳንህንም ለአግልጋይቱ ልጅ ለእኔ ስጥ።
እንደገና ይራራልናል፤ በደሎቻችንን ይረጋግጣል፥ ኃጢአታቸውን ሁሉ በባሕሩ ጥልቅ ትጥላለህ።