La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 25:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱ እግሮቼን ከወጥመድ ያወጣቸዋልና ዐይኖቼ ሁልጊዜ ወደ ጌታ ናቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዐይኖቼ ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር ናቸው፤ እግሮቼን ከወጥመድ የሚያላቅቃቸው እርሱ ነውና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከወጥመዶች ሁሉ ስለሚያድነኝ ሁልጊዜ ወደ እርሱ እመለከታለሁ።

Ver Capítulo



መዝሙር 25:15
9 Referencias Cruzadas  

አሁንም፥ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ከአንተ በኋላ በጌታዬ በንጉሥ ዙፋን ላይ የሚቀመጠውን ትነግራቸው ዘንድ የእስራኤል ሁሉ ዐይን ይመለከትሃል።


አምላካችን ሆይ! አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን ልንቋቋመው አንችልም፤ ዐይኖቻችን ወደ አንተ ከማንሣት በቀር የምናደርገውን ነገር አናውቅም።”


እነሆ፥ የአገልጋዮች ዐይኖች ወደ ጌታቸው እጅ እንደ ሆኑ፥ የአገልጋዪቱም ዐይን ወደ እመቤትዋ እጅ እንደሆነ፥ እንዲሁ እስኪምረን ድረስ ዓይናችን ወደ ጌታ አምላካችን ነው።


አቤቱ ጌታ፥ ዐይኖቼ ወደ አንተ ናቸውና፥ በአንተ ታመንሁ፥ ነፍሴን አትተዋት።


አምባዬና መጠጊያዬ አንተ ነህና ስለ ስምህ መንገዴን አቅና ምራኝም።


በሕዝቤ መካከል ክፉዎች ሰዎች ተገኝተዋል፤ እንደ ወፍ አጥማጆችም ያደባሉ፥ ወጥመድንም ይዘረጋሉ ሰዎችንም ያጠምዳሉ።