መዝሙር 22:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ግን ትል ነኝ ሰውም አይደለሁም፥ የሰው ማላገጫ በሕዝብም ዘንድ የተናቅሁ ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያዩኝ ሁሉ ይሣለቁብኛል፤ ራሳቸውንም እየነቀነቁ እንዲህ እያሉ ይዘልፉኛል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚያዩኝ ሰዎች ሁሉ ይዘባበቱብኛል፤ ፊታቸውን ያኰሳትሩብኛል፤ ራሳቸውንም ይነቀንቁብኛል። |
እኔ ደግሞ እንደ እናንተ እናገር ዘንድ ይቻለኝ ነበር፥ ነፍሳችሁ በነፍሴ ፋንታ ቢሆን ኖሮ፥ እኔ በእናንተ ላይ ቃል ማሳካት፥ ራሴንም በእናንተ ላይ መነቅነቅ በተቻለኝ ነበር።
የእስራኤል ታዳጊ ቅዱሱም፥ ጌታ፥ ሰዎች በሚንቁት ሕዝብም ለሚጠላው፥ ለገዢዎች አገልጋይ እንዲህ ይላል፦ ‘ስለ ታማኙ ስለ ጌታ ስለ መረጠህም ስለ እስራኤል ቅዱስ ነገሥታት አይተው ይነሣሉ፥ መሳፍንትም አይተው ይሰግዳሉ።’
የእሾህ አክሊል ጐንጉነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፤ በፊቱም ተንበርክከው “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን” እያሉ አፌዙበት፤
በመንገድ የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ የስድብ ናዳ በማውረድ እንዲህ ይሉት ነበር፤ “አይ፥ ቤተ መቅደስን አፍርሰህ በሦስት ቀን የምትሠራ አንተ ነህ፤