La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 22:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታን የምትፈሩ፥ አመስግኑት፥ የያዕቆብ ዘር ሁላችሁ፥ አክብሩት፥ የእስራኤልም ዘር ሁላችሁ፥ ፍሩት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱ የተጨነቀውን ሰው ጭንቀት፣ አልናቀም፤ ቸልም አላለምና፤ ፊቱንም ከርሱ አልሰወረም፤ ነገር ግን ድረስልኝ ብሎ ሲጮኽ ሰማው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የተጨቈነውን ሰው አልናቀውም፤ በሁናቴውም አልተጸየፈውም፤ ፊቱን ከእርሱ አልሰወረም፤ ነገር ግን ለእርዳታ የሚያደርገውን ጩኸት አዳመጠው።

Ver Capítulo



መዝሙር 22:24
11 Referencias Cruzadas  

በተጨነቅሁ ጊዜ ጌታን ጠራሁት፥ መለሰልኝ፥ አሰፋልኝም።


አምላኬ፥ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከማዳንና ከጩኸቴ ለምን ራቅህ?


ወደ አንተ ጮኹ አመለጡም፥ በአንተንም ተማመኑ አላፈሩም።


ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል፥ ፊታችሁም በፍጹም አያፍርም።


አጥንቶቼ ሁሉ እንዲህ ይሉሃል፦ አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? ችግረኛን ከሚቀማው እጅ፥ ችግረኛንና ድሀውንም ከሚነጥቀው እጅ ታድነዋለህ።


አቤቱ፥ ቸርነትህ መልካም ናትና ስማኝ። እንደ ርኅራኄህም ብዛት ወደ እኔ ተመልከት፥


ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ “አባት ሆይ! ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ፤” አለ። ይህንንም ብሎ ሞተ።


እርሱም ሥጋ ለብሶ በምድር በሚመላለስ ጊዜ፥ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል፥ ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ ስለ ጻድቅ ፍርሃቱም ጸሎቱ ተሰማለት፤