ለጦርነት ኃይልን ታስታጥቀኛለህ፥ በበላዬ የቆሙትን ሁሉ በበታቼ ታስገዛቸዋለህ።
ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው እንዲሸሹ አደረግህ፤ እኔም የሚጠሉኝን አጠፋኋቸው።
ጠላቶቼ ከፊቴ ወደ ኋላ እንዲሸሹ አደረግህ የሚጠሉኝንም ሁሉ አጠፋቸዋለሁ።
ክፋትን በአንተ ላይ ዘርግተዋልና፥ የማይቻላቸውንም ምክር አሰቡ።
እንደ በደላቸውም፥ እንደ ክፋታቸውም ፍዳቸውን ይከፍላቸዋል፥ ጌታ አምላካችን ያጠፋቸዋል።