ለጌታ በምስጋና ዘምሩ፥ ለአምላካችንም በመሰንቆ ዘምሩ፥
ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፤ ለአምላካችንም በመሰንቆ ምስጋና አቅርቡ።
ለእግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር ዘምሩ፤ በገና እየደረደራችሁ ለአምላካችን ዘምሩ።
ቃሉን ልኮ ያቀልጠዋል፤ ነፋሱን ያነፍሳል፥ ውኆችንም ያፈስሳል።
መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ፥ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።
ለጌታ በመሰንቆ፥ በመሰንቆና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩ።