በፊታቸውም ባሕሩን ከፈልህ፥ በባሕሩ መካከል በደረቅ ምድር ተሻገሩ፤ አሳዳጆቻቸውን ግን በኃይለኛ ውኃ እንደሚጣል ድንጋይ ወደ ጥልቁ ጣልካቸው።
መዝሙር 106:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀይ ባሕርን ገሠጸው፥ እርሱም ደረቀ፥ እንደ ምድረ በዳ በጥልቁ መራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀይ ባሕርን ገሠጸ፤ እርሱም ደረቀ፤ በምድረ በዳ እንደሚታለፍ በጥልቅ ውሃ መካከል መራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀይ ባሕርን በገሠጸው ጊዜ ደረቀ፤ ጥልቁን ውሃ እንደ በረሓ አድርጎ ሕዝቦቹን እየመራ አሻገራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተራበችን ነፍስ አጥግቦአልና፥ የተራቈተችንም ነፍስ በበረከት ሞልቶአልና። |
በፊታቸውም ባሕሩን ከፈልህ፥ በባሕሩ መካከል በደረቅ ምድር ተሻገሩ፤ አሳዳጆቻቸውን ግን በኃይለኛ ውኃ እንደሚጣል ድንጋይ ወደ ጥልቁ ጣልካቸው።
በመጣሁስ ጊዜ ሰው ስለምን አልነበረም? በጠራሁስ ጊዜ የሚመልስ ስለምን አልነበረም? መታደግ እንዳትችል እጄ አጭር ሆናለችን? ወይስ ለማዳን ኃይል የለኝም? እነሆ፥ በገሠጽሁ ጊዜ ባሕርን አደርቃለሁ፥ ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋቸዋለሁ፤ ውኃም አጥተው ዓሦቻቸው ይገማሉ፥ በጥማትም ይሞታሉ።