መዝሙር 102:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባዘነና ልመናውን በጌታ ፊት ባፈሰሰ ጊዜ የችግረኛ ጸሎት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴም ወደ አንተ ይድረስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ! የአንተን ርዳታ በመፈለግ ስጮኽም አድምጠኝ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሴ፥ እግዚአብሔርን ታመሰግነዋለች። አጥንቶቼም ሁሉ የተቀደሰ ስሙን። |
ከብዙ ቀኖች በኋላ የግብጽ ንጉሥ ሞተ፤ የእስራኤልም ሕዝቦች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፥ ጮኹም፥ ስለባርነታቸውም የልመና ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ።
እርሱም ሥጋ ለብሶ በምድር በሚመላለስ ጊዜ፥ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል፥ ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ ስለ ጻድቅ ፍርሃቱም ጸሎቱ ተሰማለት፤
“ነገ በዚህ ጊዜ ከብንያም ምድር አንድ ሰው ወደ አንተ እልካለሁ፤ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ እንዲሆን ቀባው፤ እርሱም ሕዝቤን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ይታደጋል። እነሆ፤ ሕዝቤን ከላይ ተመልክቻለሁ፤ የስቃይ ጩኸቱ ከእኔ ዘንድ ደርሷልና።”