ወደ ሀብታሙም ቤት እንግዳ መጣ፤ ሀብታሙ ግን ከራሱ በጎች ወይም ቀንድ ከብቶች ወስዶ ለመጣበት እንግዳ ምግብ ማዘጋጀት አልፈለገም፤ የድኻውን ግልገል ወስዶ ቤቱ ለመጣው እንግዳ አዘጋጀው።”
ምሳሌ 5:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ተወደደች ዋላ እንደ ተዋበችም ሚዳቋ፥ ጡትዋ ሁልጊዜ ታርካህ፥ በፍቅርዋም ሁልጊዜ ጥገብ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷ እንደ ተወደደች ዋላ፣ እንደ ተዋበች ሚዳቋ ናት፤ ጡቶቿ ዘወትር ያርኩህ፤ ፍቅሯም ሁልጊዜ ይማርክህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ተወደደች ዋላ እንድ ተዋበችም ሚዳቋ ትሁንልህ፤ ውበትዋ ሁልጊዜ ያርካህ፤ በፍቅርዋም ዘወትር ደስ ይበልህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዋሊያና በውርንጭላ ፍቅር፥ ከሚስትህ ጋር ተፋቀር፥ የፍቅርዋ ሞገስ ያርካህ፥ ለአንተ ትሁንህ፥ ሁልጊዜም ከአንተ ጋር ትኑር፤ በዚች ፍቅር ስትፋቀር ብዙ ትሆናለህ። |
ወደ ሀብታሙም ቤት እንግዳ መጣ፤ ሀብታሙ ግን ከራሱ በጎች ወይም ቀንድ ከብቶች ወስዶ ለመጣበት እንግዳ ምግብ ማዘጋጀት አልፈለገም፤ የድኻውን ግልገል ወስዶ ቤቱ ለመጣው እንግዳ አዘጋጀው።”