ሌላውን ወንድማችሁንና ብንያምን ይዛችሁ ለመመለስ እንድትችሉ ሁሉን የሚችል አምላክ በምሕረቱ የዚያን ሰው ልብ ያራራላችሁ። እንግዲህ ልጆቼንም ባጣ ምን አደርጋለሁ፤ ያመጣውን እቀበላለሁ።”
ምሳሌ 29:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዙ ሰዎች የሹምን ፊት ይሻሉ፥ የሰው ፍርድ ግን ከጌታ ዘንድ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙዎች በገዥ ፊት ተደማጭነት ማግኘት ይሻሉ፤ ሰው ፍትሕ የሚያገኘው ግን ከከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙ ሰዎች የባለሥልጣንን ርዳታ ይፈልጋሉ፤ ፍትሕ የሚገኘው ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ ነው። |
ሌላውን ወንድማችሁንና ብንያምን ይዛችሁ ለመመለስ እንድትችሉ ሁሉን የሚችል አምላክ በምሕረቱ የዚያን ሰው ልብ ያራራላችሁ። እንግዲህ ልጆቼንም ባጣ ምን አደርጋለሁ፤ ያመጣውን እቀበላለሁ።”
ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባርያህን ጸሎት፥ ስምህን በመፍራት የሚደሰቱትን የባርያዎችህን ጸሎት ያድምጥ፤ ዛሬ ለባርያህ እባክህን አከናውንለት፥ በዚህም ሰው ፊት ሞገስን ስጠው። እኔም የንጉሡ ጠጅ አሳላፊ ነበርኩ።
እኔ ግን፦ “በከንቱ ደከምሁ፥ ምንም ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ጉልበቴን ፈጀሁ፤ ፍርዴ ግን በጌታ ዘንድ፥ ዋጋዬም በአምላኬ ዘንድ ነው” አልኩ።