ሕግን የሚጠብቅ አስተዋይ ልጅ ነው፥ ራሳቸውን የማይቆጣጠሩትን የሚከተል ግን አባቱን ያሳፍራል።
ሕግን የሚጠብቅ አስተዋይ ልጅ ነው፤ ከሆዳሞች ጋራ ጓደኛ የሚሆን ግን አባቱን ያዋርዳል።
ሕግን የሚያከብር ልጅ ጥበበኛ ነው፤ ከማይረቡ ወስላቶች ጋር ወዳጅ የሚሆን ልጅ ግን አባቱን ያሳፍራል።
አባቱን የሚያስከፋ እናቱንም የሚያሳድድ የሚያሳፍርና ጐስቋላ ልጅ ነው።
ከአባቱና ከእናቱ እየሰረቀ፦ “አላጠፋሁም” የሚል የአጥፊ ሰው ባልንጀራ ነው።
በትርና ተግሣጽ ጥበብን ይሰጣሉ፥ ያልተቀጣ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል።
ጥበብን የወደደ ሰው አባቱን ደስ ያሰኛል፥ አመንዝሮችን የሚከተል ግን ሀብቱን ያጠፋል።
ከጥቂት ቀንም በኋላ ታናሹ ልጅ ገንዘቡን ሁሉ ሰብስቦ ወደ ሩቅ አገር ሄደ፤ ከዚያም እያባከነ ገንዘቡን በተነ።
ነገር ግን ይህ ልጅህ ገንዘብህን ከአመንዝራ ሴቶች ጋር አባክኖ በመጣ ጊዜ፥ የሰባውን ፍሪዳ አረድህለት፤’ አለው።