ምሳሌ 27:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቁጣ ጭካኔን ያስከትላል፥ ንዴትም እንደ ጎርፍ ነው፥ በቅንዓት ፊት ግን ማን መቆም ይችላል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንዴት ጨካኝ፣ ቍጣም ጐርፍ ነው፤ በቅናት ፊት ግን ማን መቆም ይችላል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቊጣ ጭካኔና ንዴትን ያስከትላል፤ ቅናት ግን ከቊጣ የባሰ ነው። |
አውናን ግን የሚወለደው ልጅ የእርሱን ስም የሚያስጠራ እንደማይሆን ስላወቀ፥ ከወንድሙ ሚስት ጋር ሩካቤ ሥጋ በፈጸመ ቍጥር የወንድሙንም ስም የሚያስጠራ ልጅ እንዳይወለድ ዘሩን በምድር ላይ ያፈስ ነበር።
እንደ ማኅተም በልብህ፥ እንደ ማኅተም በክንድህ አኑረኝ፥ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናትና፥ ቅንዓትም እንደ ሲኦል የጨከነች ናትና። ፍንጣሪዋ እንደ እሳት ፍንጣሪ፥ እንደ እግዚአብሔር ነበልባል ነው።
አይሁድ ግን ቀንተው ከሥራ ፈቶች ክፉ ሰዎችን አመጡ ሕዝብንም ሰብስበው ከተማውን አወኩ፤ ወደ ሕዝብም ያወጡአቸው ዘንድ ፈልገው ወደ ኢያሶን ቤት ቀረቡ፤
ከክፉው እንደነበረው ወንድሙንም እንደ ገደለው እንደ ቃየል አይደለም፤ ስለምንስ ገደለው? የእርሱ ሥራ ክፉ፥ የወንድሙ ግን ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።