የአቤሴሎምን ያኽል በመልከ መልካምነቱ የታወቀ ሰው በመላው እስራኤል ከቶ አልነበረም፤ ከራስ ጠጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ ምንም እንከን የሌለበት ሰው ነበር፤
ምሳሌ 27:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብር በእሳት ወርቅም በማቅለጫ ይፈተናል፥ ሰውም በሚያመሰገኑት ሰዎች አፍ ይፈተናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብር በማቅለጫ፣ ወርቅም በከውር እንደሚፈተን፤ ሰውም በአንደበት ምስጋና ይፈተናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወርቅና ብር በእሳት ተፈትነው ጥራታቸው እንደሚታወቅ፥ የሰውም መልካምነት የሚቀርብለትን ምስጋና በሚቀበልበት ሁኔታ ተፈትኖ ይታወቃል። |
የአቤሴሎምን ያኽል በመልከ መልካምነቱ የታወቀ ሰው በመላው እስራኤል ከቶ አልነበረም፤ ከራስ ጠጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ ምንም እንከን የሌለበት ሰው ነበር፤
አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አስገባለሁ፤ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፤ እኔም፦ “ይህ ሕዝቤ ነው” እላለሁ፥ እርሱም፦ “ጌታ አምላኬ ነው” ይላል።
ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥ የሌዊንም ልጆች ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል፤ እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቁርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ።
በዚህም በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ ነው።
የፍልስጥኤማውያን ጦር አዛዦች እንደ ወትሮው ሁሉ ለጦርነት ይወጡ ነበር፤ ዳዊትም ከቀሩት የሳኦል መኳንንት የበለጠ ድል አገኘ፤ ስሙም እጅግ የታወቀ ሆነ።