እርሷንም መከልከል ነፍስን መከልከልና ዘይትን በቀኝ እጅ መጨበጥ ነው።
እርሷን ለመግታት መሞከር፣ ነፋስን እንደ መግታት ወይም ዘይትን በእጅ እንደ መጨበጥ ነው።
ነፋስን ለማቆም ዘይትንም በእጅ ጨብጦ ለመያዝ እንደማይቻል ሁሉ እርስዋንም ዝም ማሰኘት አይቻልም።
በዝናብ ቀን የሚያንጠባጥብ ቤትና ጠበኛ ሴት አንድ ናቸው፥
ብረት ብረትን ይስለዋል፥ ሰውም ባልንጀራውን እንዲሁ።
ማርያምም ዋጋው እጅግ የከበረ የጥሩ ናርዶስ ሽቶ ንጥር ወስዳ የኢየሱስን እግሮች ቀባች፤ በጠጉርዋም አበሰቻችው፤ ቤቱም በሽቶው መዓዛ ተሞላ።