ለላኩት የታመነ መልእክተኛ፥ በመከር ወራት ደስ እንዲሚያሰኝ የውርጭ ጠል ነው፥ የጌታውን ነፍስ ያሳርፋልና።
በመከር ጊዜ የበረዶ ቅዝቃዜ ለሰስ እንደሚያደርግ ሁሉ፣ ታማኝ መልእክተኛም ለላኩት እንደዚሁ ነው፤ የጌቶቹን መንፈስ ያሳርፋልና።
ቀዝቃዛ ውሃ በሙቀት ጊዜ የሚያረካውን ያኽል ታማኝ መልእክተኛም የላከውን ሰው ያረካል።
መጥፎ መልእክተኛ በክፉ ላይ ይወድቃል፥ የታመነ መልእክተኛ ግን ፈውስ ነው።
የቀዘቀዘ ውኃ ለደረቀ ጉሮሮ ደስ እንደሚያሰኝ፥ ከሩቅ አገር የመጣ መልካም ምሥራች እንዲሁ ነው።
በሞኝ አማካኝነት መልእክት የሚልክ፥ እግሮቹን ይቈርጣል፥ ግፍንም ይጠጣል።
የካህኑም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስና አለቆቹ ከሮቤል ልጆችና ከጋድ ልጆች ዘንድ ከገለዓድ አገር ወደ ከነዓን አገር ወደ እስራኤል ልጆች ተመለሱ፥ ወሬም ይዘውላቸው መጡ።