አባትህና እናትህ ደስ ይበላቸው፥ አንተንም የወለደች ደስ ይበላት።
አባት እናትህ ደስ ይበላቸው፤ ወላጅ እናትህም ሐሤት ታድርግ።
አባትህና እናትህ በአንተ ደስ ይበላቸው፤ እናትህም በአንተ ሐሤት ታድርግ።
አባትህና እናትህ በአንተ ደስ ይላቸዋል፥ አንተንም የወለደች ደስ ይላታል።
የሰሎሞን ምሳሌዎች። ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፥ አላዋቂ ልጅ ግን ለእናቱ ኀዘን ነው።
ሰነፍ ልጅ ለአባቱ ፀፀት ነው፥ ለወለደችውም ምሬት ነው።
ልጄ ሆይ፥ ልብህ ጠቢብ ቢሆን የእኔም ልብ ደስ ይለዋል፥
ልጄ ሆይ፥ ልብህን ስጠኝ፥ ዐይኖችህም መንገዴን ይውደዱ።
ልጄ ሆይ፥ ጠቢብ ሁን፥ ልቤንም ደስ አሰኘው፥ ለሚሰድበኝ መልስ መስጠት ይቻለኝ ዘንድ።
ጎረቤቶችዋም ዘመዶችዋም ጌታ ታላቅ ምሕረቱን እንዳደረገላት ሰምተው ከእርሷ ጋር ደስ አላቸው።