ከወይን ጠጅ ጠጪዎች ጋር አትቀመጥ እንዲሁም ሥጋ ከማይጠግቡ ጋር፥
ብዙ የወይን ጠጅ ከሚጠጡ፣ ሥጋ ከሚሰለቅጡ ጋራ አትወዳጅ፤
ብዙ የወይን ጠጅ ከሚጠጡና ብዙ ምግብ ከሚበሉ ጋር ጓደኛ አትሁን፤
የወይን ጠጅ ጠጭ አትሁን፤ ለሥጋም አትሳሳ
የወይን ጠጅ ፌዘኛ ያደርጋል፥ ብርቱ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋል፥ በዚህም የሳተ ሁሉ ጠቢብ አይደለም።
ተድላ የሚወድድ ድሀ ይሆናል፥ የወይን ጠጅንና ዘይትንም የሚወድድ ሀብታም አይሆንም።
ሰውነትህም ቢጎመጅ፥ በጉሮሮህ ላይ ካራ አድርግ።
ሕግን የሚጠብቅ አስተዋይ ልጅ ነው፥ ራሳቸውን የማይቆጣጠሩትን የሚከተል ግን አባቱን ያሳፍራል።
ነገር ግን እናንተ፦ “ነገ እንሞታለንና እንብላ እንጠጣም” በማለት እነሆም፥ በሐሤትና በደስታ በሬንና በጉንም ስታርዱ፥ ሥጋንም ስትበሉ፥ የወይን ጠጅንም ስትጠጡ ነበር።
የሚያሰክር መጠጥ ፍለጋ ማልደው ለሚነሡ፤ እስኪያነዳቸውም ወይን በመጠጣት ሌሊቱን ለሚያነጉ ወዮላቸው!
የወይን ጠጅ ለመጠጣት ጀግኖች፤ የሚያሰክር መጠጥ ለመደባለቅ ብርቱ ለሆኑ ወዮላቸው!
ባልንጀሮቹን ባርያዎች መደብደብ ቢጀምር፥ ከሰካራሞችም ጋር ቢበላና ቢጠጣ፥
ከጥቂት ቀንም በኋላ ታናሹ ልጅ ገንዘቡን ሁሉ ሰብስቦ ወደ ሩቅ አገር ሄደ፤ ከዚያም እያባከነ ገንዘቡን በተነ።
“በሐምራዊና በክት ልብስ የሚሽቀረቀር አንድ ሀብታም ሰው ነበረ፤ ዕለት ዕለትም እየተመቸው በቅንጦት ይኖር ነበር።
“ነገር ግን ልባችሁ በመጠጥ ብዛትና በስካር፥ ስለ ኑሮም ማሰብ እንዳይዝል፥ ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤
በቀን እንደምንሆነው በጨዋነት እንመላለስ፤ በመሶልሶልና በስካር አይሁን፤ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፤ በክርክርና በቅናት አይሁን፤
መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ ብክነት እንደ ሆነው በወይን ጠጅ አትስከሩ፤
‘ይህ ልጃችን እልከኛና ዓመፀኛ ነው፤ አይታዘዘንም፤ አባካኝና ሰካራም ነው’ ብለው ለአለቆች ይንገሯቸው።