ኤልሳዕም መለስ ብሎ ዙሪያውን በመቃኘት፥ አተኲሮ ተመለከታቸውና በእግዚአብሔር ስም ረገማቸው፤ በዚህም ጊዜ ሁለት እንስት ድቦች ከጫካ ወጥተው ከእነዚያ ልጆች መካከል አርባ ሁለቱን ሰባብረው ጣሉአቸው።
ምሳሌ 19:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሚያፌዙ ሰዎች ፍርድ ተዘጋጅታለች፥ ለሰነፎችም ጀርባ በትር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለፌዘኞች ቅጣት፣ ለሞኞችም ጀርባ ጅራፍ ተዘጋጅቷል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለፌዘኞች ፍርድ፥ ለሞኞችም ግርፋት ተዘጋጅቶላቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለክፉዎች ሰዎች መቅሠፍት ተዘጋጅቶላቸዋል፥ ለሰነፎችም እንደዚሁ ቅጣት። |
ኤልሳዕም መለስ ብሎ ዙሪያውን በመቃኘት፥ አተኲሮ ተመለከታቸውና በእግዚአብሔር ስም ረገማቸው፤ በዚህም ጊዜ ሁለት እንስት ድቦች ከጫካ ወጥተው ከእነዚያ ልጆች መካከል አርባ ሁለቱን ሰባብረው ጣሉአቸው።
ጠቢብ ብትሆን ለራስህ ጠቢብ ትሆናለህ፥ ፌዘኛም ብትሆን ፌዘኛነትህን ለብቻህ ትሸከማለህ። (የሚቀጥለው ከግሪክ የተጨመረ ነው።) ልጄ ለራስህ አዋቂ ብትሆን ለባልንጀራህም አዋቂ ትሆናለህ፥ ለራስህ ክፉ ብትሆን ግን ክፋትን ለብቻህ ትሸከማለህ። ሐሰትን የሚያዘጋጅ ሰው ነፋሳትን እንደሚገዛ ነው፥ የሚበርር ወፍንም እንደሚከተል ይመስላል። የወይኑ ቦታ መንገዱን ረስቷልና፥ የሚሠማራባትን መንገድ እንዲስት አድርጓልና፥ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፥ ለጥም ወደ ተሠራች አገር ይሄዳል፥ የማያፈራ የማይጠቅም ገንዘብንም በእጁ ይሰበስባል።