ከነቢያቱም አንዱ ጎመን የሚመስል ቅጠላ ቅጠል ለመልቀም ወደ ሜዳ ሔደ፤ እርሱም በዱር ውስጥ የበቀለ የቅል ሐረግ አገኘ፤ መሸከም የሚችለውን ያኽል በርከት ያለ ቅል ቆርጦ አመጣ፤ የዚያንም ምንነት ሳያውቅ ከትፎ ወጡ ውስጥ ጨመረው፤
ምሳሌ 19:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፍስ እውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም፥ እግሩንም የሚያፈጥን ከመንገድ ይስታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕውቀት አልባ የሆነ ቀናኢነት መልካም አይደለም፤ ጥድፊያም መንገድን ያስታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕውቀት ያልተጨመረበት ትጋት ጠቃሚ አይደለም፤ በችኰላ የሚሮጥ ሰው መንገዱን ይስታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍስ ዕውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ እግሩንም የሚያፈጥን ከመንገድ ይስታል። |
ከነቢያቱም አንዱ ጎመን የሚመስል ቅጠላ ቅጠል ለመልቀም ወደ ሜዳ ሔደ፤ እርሱም በዱር ውስጥ የበቀለ የቅል ሐረግ አገኘ፤ መሸከም የሚችለውን ያኽል በርከት ያለ ቅል ቆርጦ አመጣ፤ የዚያንም ምንነት ሳያውቅ ከትፎ ወጡ ውስጥ ጨመረው፤
ጫፎችዋ በደረቁ ጊዜ ይሰበራሉ፥ ሴቶችም መጥተው ያቃጥሉአቸዋል፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና ፈጣሪው አይራራለትም፤ ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ የተፈተነውን፥ የከበረውን፥ መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ፤ “የሚያምን አያፍርም።”
ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ትተሃልና ለእኔ ካህን እንዳትሆን ትቼሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።