La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 18:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ብዙ ወዳጆች ያሉት ሰው ይጠፋል፥ ነገር ግን ከወንድም አብልጦ የሚጠጋጋ ወዳጅ አለ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወዳጅ የሚያበዛ ሰው ራሱን ለጥፋት ይዳርጋል፤ ነገር ግን ከወንድም አብልጦ የሚቀርብ ጓደኛም አለ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወዳጆች ሳይሆኑ ወዳጆች መስለው የሚታዩ አሉ፤ እውነተኛ ወዳጅ ግን ከወንድም ይበልጣል።

Ver Capítulo



ምሳሌ 18:24
17 Referencias Cruzadas  

ወንድሜ ዮናታን ሆይ፤ እኔ ስለ አንተ አዘንሁ፤ አንተ ለእኔ እጅግ ውድ ነበርህ፤ ፍቅርህ ለእኔ ድንቅ ነበረ፤ ከሴት ፍቅርም ይልቅ የበረታ ነበር።


ኢታይ ግን፥ “በሕያው ጌታ ስም እምላለሁ! እንዲሁም በጌታዬ በንጉሡ እምላለሁ፤ ሕይወትም ይሁን ሞት በየትም ቦታ ንጉሥ ጌታዬ የሚሆነውን ሁሉ አገልጋይህም እንደዚያው እሆናለሁ” ብሎ መለሰለት።


አቤሴሎምም፥ ሑሻይን፥ “ለወዳጅህ ያለህ ታማኝነት እስከዚህ ድረስ ነው? ለምን ከወዳጅህ ጋር አልሄድህም?” ሲል ጠየቀው።


ንጉሥ ዳዊት በራሱና በሳኦል ልጅ በዮናታን መካከል በጌታ ፊት ስላደረጉት መሐላ ሲል የሳኦልን ልጅ፥ የዮናታንን ልጅ መፊቦሼትን ከሞት አተረፈ።


ወዳጅ በዘመኑ ሁሉ ይወድዳል፥ ወንድምም ለመከራ ይወለዳል።


ወዳጅህንና የአባትህን ወዳጅ አትተው፥ በመከራህም ቀን ወደ ወንድምህ ቤት አትግባ፥ የቀረበ ወዳጅ ከራቀ ወንድም ይሻላል።


ሽቱና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፥ ነፍስም በወዳጅ ምክር ደስ ይላታል።


ዳዊት ከሳኦል ጋር የሚያደርገውን ንግግር እንዳበቃ፤ የዮናታን ነፍስ ከዳዊት ነፍስ ጋር ተቆራኘች፤ እንደራሱም አድርጎ ወደደው።


ዮናታን እንደ ራሱ አድርጎ ስለ ወደደው ከዳዊት ጋር ኪዳን አደረገ፤