ምሳሌ 16:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓይኑን የሚዘጋ ጠማማ አሳብን ያስባል፥ ከንፈሩን የሚነክስ ክፋትን ይፈጽማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዐይኑ የሚጠቅስ ሰው ጠማማነትን ያውጠነጥናል፤ በከንፈሩ የሚያሽሟጥጥም ወደ ክፋት ያዘነብላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐይኑን በሰው ላይ የሚጠቅስ ተንኰልን ያቀደ ነው፤ ከንፈሩንም የሚነክስ ወደ ክፋት የሚያመራ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዐይኑ ትኩር ብሎ የሚመለከት፥ ጠማማ ዐሳብን ያስባል፤ በከንፈሩም ክፉውን ሁሉ የሚያደርግ የክፋት ምድጃ ነው። |
የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፤ ጆሮአቸውን ድፈን፤ ዐይኖቻቸውንም ክደን፤ ይህ ካልሆነማ፤ በዐይናቸው አይተው፤ በጆሮአቸው ሰምተው፤ በልባቸውም አስተውለው በመመለስ ይፈወሳሉ።”
እጆቻቸው ክፉ ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ልዑሉና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፤ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጉናሉ።
በዓይናቸው አይተው፥ በጆሮአቸው ሰምተው፥ በልባቸውም አስተውለው፥ ተመልሰው እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል፥ ጆሮአቸው ደንቁሮአል፥ ዓይናቸውም ተጨፍኖአል፤