ምሳሌ 16:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሠራተኛን የዕለት ጉርስ ፍላጎቱ ታታሪ ያደርገዋል፥ ረሀቡ ይጐተጉተዋልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሠራተኛን የዕለት ጕርስ ፍላጎቱ ታታሪ ያደርገዋል፤ ራቡም ይገፋፋዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውን ጠንክሮ እንዲሠራ የሚያደርገው የምግብ ፍላጎቱ ነው፤ ራብ ደግሞ ለሥራ ይገፋፋዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰው በድካሙ ለራሱ ይደክማል፥ ከራሱም ጥፋትን ያርቃል። ጠማማ ግን በአፉ ጥፋትን ይለብሳል። |
ጠቢብ ብትሆን ለራስህ ጠቢብ ትሆናለህ፥ ፌዘኛም ብትሆን ፌዘኛነትህን ለብቻህ ትሸከማለህ። (የሚቀጥለው ከግሪክ የተጨመረ ነው።) ልጄ ለራስህ አዋቂ ብትሆን ለባልንጀራህም አዋቂ ትሆናለህ፥ ለራስህ ክፉ ብትሆን ግን ክፋትን ለብቻህ ትሸከማለህ። ሐሰትን የሚያዘጋጅ ሰው ነፋሳትን እንደሚገዛ ነው፥ የሚበርር ወፍንም እንደሚከተል ይመስላል። የወይኑ ቦታ መንገዱን ረስቷልና፥ የሚሠማራባትን መንገድ እንዲስት አድርጓልና፥ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፥ ለጥም ወደ ተሠራች አገር ይሄዳል፥ የማያፈራ የማይጠቅም ገንዘብንም በእጁ ይሰበስባል።