ምሳሌ 16:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች፥ ፍጻሜዋ ግን የሞት መንገድ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሰው ቀና መስሎ የሚታይ መንገድ አለ፤ በመጨረሻ ግን ወደ ሞት ያደርሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሰው ትክክለኛ መስሎ የሚታይ መንገድ አለ፤ በመጨረሻ ግን ወደ ሞት ያመራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች፤ ፍጻሜዋ ግን የሲኦል ጕድጓዶችን ይመለከታል። |
በእምነት እንደምትኖሩ ለማወቅ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ካልሆናችሁ በቀር፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ አታውቁም ኖሯል?