ምሳሌ 15:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጠቢባን ከንፈር እውቀትን ትዘራለች፥ የሰነፎች ልብ ግን እንዲህ አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጠቢባን ከንፈር ዕውቀትን ታስፋፋለች፤ የሞኞች ልብ ግን እንዲህ አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕውቀት የሚስፋፋው በብልኆች እንጂ በሞኞች አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጠቢባን ከንፈሮች በዕውቀት የታሰሩ ናቸው፤ የሰነፎች ልብ ግን የጸና አይደለም። |
ምላስም እንደ እሳት ናት፤ በሰውነት ክፍሎቻችን መካከል የምትገኝ የክፋት ዓለም ናት፤ ሰውነትን ሁሉ ታረክሳለች፤ ደግሞም የፍጥረትን ሩጫ ታቃጥላለች፤ ራሷም በገሃነም ትቃጠላለች።