ምሳሌ 10:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ ነገር ማድረግ ለአላዋቂ ጨዋታ ነው፥ እንዲሁም ጥበብ ለአስተዋይ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞኝ ሰው በክፉ ተግባር ይደሰታል፤ አስተዋይ ሰው ግን በጥበብ ደስ ይለዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስሕተት በማድረግ መደሰት ሞኝነት ነው፤ በአእምሮ የበሰሉ ሰዎች ደስ የሚላቸው ጥበብን በማግኘት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰነፍ ሰው በመሳቁ ክፉን ይሠራል፤ ጥበብ ግን ለሰው ዕውቀትን ትወልዳለች። |
አንተ ጐበዝ፥ በጉብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጉብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ ዐይኖችህም በሚያዩት ሂድ፥ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ እወቅ።