የጻድቅ አፍ የሕይወት ምንጭ ማፍለቂያ ናት፥ የክፉዎች አፍ ግን ዐመፅን ይሸፍናል።
የጻድቅ አንደበት የሕይወት ምንጭ ናት፤ መዓት ግን የክፉዎችን አፍ ይዘጋል።
የደግ ሰው ንግግር የሕይወት ምንጭ ነው፤ የክፉ ሰው ንግግር ግን የዐመፅ መሸፈኛ ነው።
የሕይወት ምንጭ በጻድቃን አፍ ነው፥ የኃጥኣንን አፍ ግን ጥፋት ይከድነዋል።
ቅኖች ያያሉ፥ ደስም ይላቸዋል፥ ክፋት በሙሉ አፉን ይዘጋል።
የጻድቅ ከንፈሮች ደስ የሚያሰኝ ነገርን ያውቃሉ፥ የክፉዎች አፍ ግን ጠማማ ነገር ይናገራል።
በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ነው፥ የክፉዎች አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል።
ሰው ከሞት ወጥመድ ያመልጥ ዘንድ የጠቢብ ሰው ትምህርት የሕይወት ምንጭ ነው።
ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፥ የጠማማ ምላስ ግን ነፍስን ይሰብራል።
የጠቢባን ከንፈር እውቀትን ትዘራለች፥ የሰነፎች ልብ ግን እንዲህ አይደለም።
የሰው አፍ ቃል የጠለቀ ውኃ ነው፥ የጥበብም ምንጭ ፈሳሽ ወንዝ ነው።
ወርቅና ብዙ ቀይ ዕንቁ ይገኛል፥ የእውቀት ከንፈር ግን የከበረች ጌጥ ናት።
እንደ አስፈላጊነቱ፥ ለሚሰሙት ጸጋን እንዲሰጥ፥ ለማነጽ የሚጠቅም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ።