ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ፦ “እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በምሄድባትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ፥ የምበላውንም እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥
ፊልጵስዩስ 4:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን ስል ስለሚያስፈልገኝ ነገር እያማረርሁ አይደለም፤ ያለኝ ነገር ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን የምለው ስለ ቸገረኝ አይደለም፤ ምክንያቱም በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ያለኝ ይበቃኛል ማለትን፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም ይህን የምለው ለኑሮዬ የሚያስፈልገኝን በማጣቴ አይደለም፤ እኔማ “ያለኝ ነገር ይበቃኛል” ማለትን ተምሬአለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም የምል ስለ አጣሁ አይደለም፤ ያለኝ እንደሚበቃኝ አውቃለሁና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና። |
ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ፦ “እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በምሄድባትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ፥ የምበላውንም እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥
ወታደሮችም እንዲሁ፦ “እኛስ ምን እናድርግ?” ብለው ይጠይቁት ነበር። እርሱም፦ “ማንንም በግፍ ወይም በሐሰት ክስ አትበዝብዙ፤ ደመወዛችሁም ይብቃችሁ፤” አላቸው።
የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ ታውቃላችሁ፤ ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች እንድትሆኑ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ።
አዎን፤ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ ለማወቅ ስል ሁሉ ነገር ጉዳት እንደሆነ አድርጌ እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ነገሮች በማጣት ተጐዳሁ፤ እነርሱንም እንደ ጉድፍ አድርጌ ቈጠርኋቸው፤ በዚህም ክርስቶስን እንዳገኝ፥
በሰማይ የበለጠና ፍጻሜ የሌለው ሀብት እንዳላችሁ በማወቃችሁ፥ የንብረታችሁን መነጠቅ በደስታ ተቀበላችሁ፤ በእስራት ላይ የነበሩትን የስቃያቸው ተካፋይ ሆናችሁ።