La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 7:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለአንድነትም መሥዋዕት ሁለት በሬዎች፥ አምስት አውራ በጎች፥ አምስት አውራ ፍየሎች፥ አምስት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች አቀረበ፤ የሶገር ልጅ የናትናኤ መባ ይህ ነበረ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ ዐምስት አውራ በግ፣ ዐምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው ዐምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የሶገር ልጅ ናትናኤል ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች አቀ​ረበ፤ የሰ​ገር ልጅ የና​ት​ና​ኤል መባ ይህ ነበረ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለደኅንነትም መሥዋዕት ሁለት በሬዎች፥ አምስት አውራ በጎች፥ አምስት አውራ ፍየሎች፥ አምስት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች አቀረበ፤ የሶገር ልጅ የናትናኤ መባ ይህ ነበረ።

Ver Capítulo



ዘኍል 7:23
8 Referencias Cruzadas  

ሰሎሞንም ኻያ ሁለት ሺህ የቀንድ ከብቶችንና አንድ መቶ ኻያ ሺህ በጎችን የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ በዚህም ዓይነት ንጉሥ ሰሎሞንና እስራኤላውያን ሁሉ ቤተ መቅደሱ ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረጉ።


“መሥዋዕትንና የደኅንነት ቁርባንን ማቅረብ ነበረብኝ፥ ዛሬ ስእለቴን ፈጸምሁ።


ከይሳኮር የሶገር ልጅ ናትናኤል፥


በእነርሱም አጠገብ የሚሰፍሩ የይሳኮር ነገድ ይሆናሉ፤ የይሳኮርም ልጆች አለቃ የሶገር ልጅ ናትናኤል ነበረ።


ለኃጢአትም መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል፤


በሦስተኛውም ቀን የዛብሎን ልጆች አለቃ የኬሎን ልጅ ኤልያብ አቀረበ፤


በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ ወንድማችንም ጢሞቴዎስ፥