ዘኍል 23:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ባላቅም ተመለሰ፥ እነሆም፥ እርሱና የሞዓብ ሹማምንት ሁሉ በሚቃጠለው መሥዋዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ተመልሶ ሲሄድ ባላቅን ከመላው የሞዓብ አለቆች ጋራ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አገኘው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም ተመልሶ ሲሄድ ባላቅ ከሞአብ መሪዎች ሁሉ ጋር ሆኖ በዚያው በሚቃጠለው መሥዋዕት አጠገብ እንደ ቆመ አገኘው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እርሱም ተመለሰ፤ እነሆም፥ እርሱና የሞዓብ አለቆች ሁሉ በመሥዋዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ ወደ እርሱ መጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ እርሱም ተመለሰ፥ እነሆም፥ እርሱና የሞዓብ አለቆች ሁሉ በመሥዋዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር። |
በለዓምም ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “ባላቅ ከአራም አመጣኝ፥ የሞዓብ ንጉሥ ከምሥራቅ ተራሮች፤ ‘ና፥ ያዕቆብን ርገምልኝ፤ ና፥ እስራኤልን አውግዝልኝ አለኝ።’