La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 18:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እናንተም ቤተ ሰቦቻችሁም፥ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያገለገላችሁበት የድካማችሁ ዋጋ ነውና በሁሉ ስፍራ ትበሉታላችሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የቀረው ግን በመገናኛው ድንኳን ለሰጣችሁት አገልግሎት ደመወዛችሁ ስለ ሆነ፣ እናንተና ቤተ ሰዎቻችሁ በየትኛውም ስፍራ ልትበሉት ትችላላችሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እርሱ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለምትሰጡት አገልግሎት የድካም ዋጋችሁ ስለ ሆነ የተረፈውንም እናንተና ቤተሰቦቻችሁ በየትኛውም ስፍራ ሆናችሁ መመገብ ትችላላችሁ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እና​ን​ተም ቤተ ሰቦ​ቻ​ች​ሁም፥ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ የማ​ገ​ል​ገ​ላ​ችሁ ዋጋ ነውና በሁሉ ስፍራ ትበ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እናንተም ቤተ ሰቦቻችሁም፥ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የማገልገላችሁ ዋጋ ነውና በሁሉ ስፍራ ትበሉታላችሁ።

Ver Capítulo



ዘኍል 18:31
9 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ እነርሱን እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ‘ከእርሱ የተመረጠውን ባቀረባችሁ ጊዜ ከአውድማው እህልና ከወይን መጭመቂያው እንደ ተገኘ ምርት ለሌዋውያን ይቈጠራል።


የተመረጠውንም ከእርሱ ባቀረባችሁ ጊዜ ስለ እርሱ ኃጢአትን አትሸከሙም፤ እንዳትሞቱም የእስራኤልን ልጆች የተቀደሱ ነገሮች አታረክሱም።’ ”


ለመንገዳችሁ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አትያዙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና።


ለሠራተኛ ደሞዙ ይገባዋልና እነርሱ የሚሰጡአችሁን እየበላችሁና እየጠጣችሁ በዚያው ቤት ተቀመጡ። ከቤት ወደ ቤት አትዘዋወሩ።


እኔ ራሴ ሸክም ሆኜባችሁ ካልሆነ በቀር፥ ከሌላ ቤተ ክርስቲያን በምን አንሳችሁ ነው? ይህን በደሌን ይቅር በሉልኝ።


ቃሉን የሚማር መልካሙን ነገር ሁሉ ከሚያስተምረው ጋር ይካፈል።