በሕዝቡ ላይ ሁልጊዜ ይፍረዱ፤ ትልቁን ነገር ሁሉ ወደ አንተ ያምጡት፥ ትንሹንም ነገር ሁሉ እነርሱ ይፍረዱ፤ እነርሱም ከአንተ ጋር ሸክሙን ይሸከማሉ፥ ለአንተም ይቀልልሃል።
ዘኍል 15:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንጨትም ሲለቅም ያገኙት ሰዎች ወደ ሙሴና ወደ አሮን ወደ ማኅበሩም ሁሉ አመጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕንጨት ሲለቅም ያገኙትም ሰዎች ሰውየውን ወደ ሙሴ፣ ወደ አሮንና ወደ መላው የእስራኤል ማኅበር አመጡት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የያዙትም ሰዎች መላው ማኅበር ወዳለበት ወደ ሙሴና ወደ አሮን ወሰዱት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰንበት ቀን ዕንጨት ሲለቅም ያገኙትም ሰዎች ወደ ሙሴና ወደ አሮን፥ ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ አመጡት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንጨትም ሲለቅም ያገኙት ሰዎች ወደ ሙሴና ወደ አሮን ወደ ማኅበሩም ሁሉ አመጡት። |
በሕዝቡ ላይ ሁልጊዜ ይፍረዱ፤ ትልቁን ነገር ሁሉ ወደ አንተ ያምጡት፥ ትንሹንም ነገር ሁሉ እነርሱ ይፍረዱ፤ እነርሱም ከአንተ ጋር ሸክሙን ይሸከማሉ፥ ለአንተም ይቀልልሃል።