La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሚክያስ 5:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የተቀረጹ ምስሎችህንና ሐውልቶችህን ከመካከልህ አጠፋለሁ፥ ከእንግዲህም ወዲያ ለእጅህ ሥራ አትሰግድም፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጥንቈላችሁን አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህም አታሟርቱም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

መተታችሁን አጠፋለሁ፤ ሟርተኞችም ከእንግዲህ ወዲህ በመካከላችሁ አይገኙም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

መተትንም ከእጅህ አጠፋለሁ፥ ምዋርተኞችም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆኑልህም፥

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

መተትንም ከእጅህ አጠፋለሁ፥ ምዋርተኞችም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆኑልህም፥

Ver Capítulo



ሚክያስ 5:12
14 Referencias Cruzadas  

ጣዖቶች ሁሉ ፈጽሞ ይወድማሉ።


በዚያን ቀን ሰዎች ሊያመልኳቸው ያበጇቸውን፤ የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይወረውራሉ።


ስለዚህም የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ፥ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፥ ይህም ኃጢአትን የማስወገድ ፍሬ ነው።


የቀረውንም እንጨት አምላክ አድርጎ ምስል ይቀርጽበታል፤ በፊቱም ተጐንብሶ ይሰግድበታል፤ ወደ እርሱም እየጸለየ፦ አምላኬ ነህና አድነኝ ይላል።


ቤቶችሽን በእሳት ያቃጥላሉ፥ በብዙ ሴቶችም ፊት በላይሽ ፍርድን ያደርጉብሻል፥ አመንዝራነትሽን አስተውሻለሁ፥ ከእንግዲህም በኋላ ዋጋ አትሰጪም።


በእናንተ ላይ ንጹሕ ውኃ እረጫለሁ እናንተም ትነጻላችሁ፥ ከርኩሰቶቻችሁ ሁሉ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አነጻችኋለሁ።


በዚያ ቀን ለዳዊት ቤትና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ከኃጢአትና ከርኩሰት የሚያነጻ ምንጭ ይፈልቃል።


ምድራቸውን የምታስለቅቃቸው አሕዛብ፥ መተተኞችን ወይም ሟርተኞችን ያዳምጣሉ፤ አንተ ግን ይህን እንድታደርግ ጌታ እግዚአብሔር አልፈቀደልህም።


አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛውም ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።


ውሻዎችና አስማተኞች፥ ሴሰኛዎችም፥ ነፍሰ ገዳዮችም፥ ጣዖት አምላኪዎችም፥ ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ ይቀራሉ።