ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፥” ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው።
ማቴዎስ 25:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ሁለት ታላንት የተቀበለው ሁለት አተረፈ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለት መክሊት የተቀበለውም እንዲሁ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፈ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ። |
ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፥” ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው።
እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክና የሚፈራ ለሕዝብም እጅግ ምጽዋት የሚያደርግ ወደ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ የሚጸልይ ነበረ።
እንዲሁም ልጆችን በማሳደግ፥ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት፥ በበጎም ሥራ ሁሉ በመትጋት፥ በመልካም ሥራዎችዋ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።