ማቴዎስ 25:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእያንዳንዱ እንደ ችሎታው፥ ለአንዱ አምስት መክሊት፥ ለአንዱ ሁለት፥ ለአንዱ ደግሞ አንድ ሰጠና ወዲያውኑ ወደ ሌላ አገር ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእያንዳንዱ እንደ ችሎታው በመደልደል ለአንዱ ዐምስት ታላንት፣ ለሌላው ሁለት፣ ለሌላው ደግሞ አንድ ታላንት ሰጥቶ ጕዞውን ቀጠለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌትዮው ለእያንዳንዱ እንደ ችሎታው በማካፈል፥ ለአንዱ አምስት መክሊት፥ ለአንዱ ሁለት መክሊት፥ ለአንዱ ደግሞ አንድ መክሊት ሰጠና ወደ ሌላ አገር ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእያንዳንዱ እንደ ዐቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ። |
“ሌላም ምሳሌ ስሙ፤ የወይን አትክልት የተከለ አንድ የእርሻ ባለቤት ነበረ፤ እርሱም ቅጥር ቀጠረለት፤ መጭመቂያም ማሰለት፤ ግንብም ሠራለት፤ እርሻውንም ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።
ያላወቀ ግን መገረፍ የሚገባውንም ያደረገ ጥቂት ይገረፋል። ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል፤ ብዙ አደራም ከተሰጠው ከእርሱ አብዝተው ይሹበታል።