ማቴዎስ 23:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መሪዎች ተብላችሁ አትጠሩ፥ መሪአችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መምህራችሁ አንዱ ክርስቶስ ስለ ሆነ፣ ‘መምህር’ ተብላችሁ አትጠሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሊቃችሁ ክርስቶስ ብቻ ስለ ሆነ ‘ሊቃውንት’ ተብላችሁ አትጠሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና ‘ሊቃውንት’ ተብላችሁ አትጠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና፦ ሊቃውንት ተብላችሁ አትጠሩ። |
እርሱም እንዲህ አለ “ወደ ከተማ ወደ አንድ ሰው ሄዳችሁ ‘መምህሩ እንዲህ ይላል፥ ጊዜዬ ቀርቦአል፤ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን በአንተ ቤት አደርጋለሁ ይላል’ በሉት።”